የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘመናዊ ሥርዓትና ኮንቴይነሮች
የ ኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ከ14 ሺህ በላይ የተለያዩ ዓይነት ኮንቴይነሮችን በመጠቀም ዕቃዎችን ከመነሻ ወደብ እስከ መዳረሻ በባሕርና በየብስ በተቀናጀ አሠራር በማጓጓዝ ለደንበኞቹ ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ተቋሙ ዘመናዊ የ Warehouse Management System በመተግበር ባዶ ኮንቴይነሮችን ለጭነት ዝግጁ የማድረግ ሂደትን አቀላጥፎ፣ በደንበኞች እጅ ያሉ ኮንቴይነሮች በወቅቱ እንዲመለሱና ለተገቢው አገልግሎት እንዲውሉ እያደረገ ነው። ይህ ዘመናዊ ሥርዓት ኮንቴይነሮች በየትኛው ወደብ፣ ተርሚናል፣ የደንበኛ መጋዘን ወይም በጉዞ ላይ እንዳሉ በቀላሉ ለመከታተል ያስችላል። በተጨማሪም በቻይና፣ ህንድ እና በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በተዘጋጁ የኮንቴይነር ዲፖዎች አማካኝነት ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል። ኮንቴይነሮች ከዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች እስከ ግንባታ ግብዓቶች፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እስከ ፋብሪካ ግብዓቶች እንዲሁም በሙቀትና በቅዝቃዜ ልዩ ሁኔታ የሚጓጓዙ ዕቃዎችን በደህና ወደ መዳረሻቸው ለማድረስ ዋና የሎጅስቲክስ መፍትሔ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።


Leave a Comment