የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በተካሄደበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከዕቅድ በላይ ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚ ው አክለውም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የድርጅቱ የኦፕሬሽን አገልግሎት መጠን ማሳደግ ተችሏልም ብለዋል። ለውጤታማነቱም በዋናነት የስምሪትና ቁጥጥር ሥራዎች በቴክኖሎጂ መታገዝ፣ ሀገር አቋራጭ የመርከብ ንግድ ሥራዎች መስፋፋትና ወጪን የቀነሰ አሰራር መከተል ለውጤታማነቱ ምክኒያት መሆኑን አስቀምጠዋል፡፡ የመርከቦችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም በመጨመር ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰራቱን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ማጎልበት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በትኩረት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው በቀጣይም ወቅቱን የዋጀ የአገልግሎት በመስጠት እና የደንበኞችን አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ውጤታማነታችንን የማላቅ ስራ እንሰራለን ብለዋል፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች በበኩላቸው የዘጠኝ ወራቱን የዕቅድ አፈጻጸም ተከትሎ በተገኘው ውጤት መደሰታቸውን ገልፀው በቀሪዎቹ ሶስት ወራት በአፈጻጸም ግምገማው ላይ በክፍተት የተነሱትን በማረምና በጥንካሬ የተነሱትን በማጎልበት ለተሻለ ውጤት እንደሚተጉ ከከፍተኛ አመራሩ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል።