Happy Mawlid Festivity to all ESL customers and Employees

በሀገራችንና እና በውጭ ሀገራት ኢባትሎ በሚሰራባቸው የስራ መስኮች ላይ ተሰማርታችሁ ሀገራችሁን በባሕር ትራንስፖርት፣ በየብስ ትራንስፖርት፣ በጅቡቲ ኤም ቲ ኤስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ በተለያዩ ወደቦች፣ በዋና መ/ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፎቻችን እያገለገላችሁ የምትገኙ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞቻችን፣ ክቡራን ወኪሎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና ለመላ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። የመውሊድ በዓል ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳስተማሩት መተሳሰብ ፣ፍቅር፣ ወንድማማችነት እና እህታማማችነት ፍቅር እንዲጎለብት ያለው ለሌለው እንዲያካፍል ነው፡፡ በመሆኑም በዓለም ደረጃ የምንታወቅበትን ብዝሃነትን ለሌሎች ምሳሌና አስተምህሮ ሊውል በሚችል መልኩ ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነታችንን በመጠበቅ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንነሳ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ::
በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ!
ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ፈጣሪ ይባርክ!
መልካም በዓል፣ ኢድ ሙባረክ !
በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ