ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
ኢትዮጵያ ወደብ ለማልማት ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ታሪካዊ ስምምነት እንዳስደሰታቸው የኢባትሎ ዋ/ሥ/አስፈፃሚ እና የድርጅቱ ሰራተኞች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያና ሶማሌ ላንድ ያደረጉት ስምምነት ለዘመናት ኢትዮጵያ ላይ የተቆለፈውን በር የከፈተ ስምምነት እንደሆነ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋ/ሥ/አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን እና ለድርጅቱ አመራር እና ሠራኞች ገልጸዋል፡፡ በተለይ ድርጅታችን ባሕር ላይ የሚሰራ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን የተደረሰው ስምምነት ትርጉሙ ብዙ ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚው በተለይ በንግድ እንቅስቃሴው ውስጥ ያሉ የትራንስፖርት ዋጋ እና አላስፈላጊ ወጪን የሚቀንስ፣ የንግድ እንቅስቃሴውን የሚጨምር፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያመጣ፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናከር ብሎም ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ ወደብ የማልማት ስራው ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ዋ/ስራ አስፈፃሚው ጨምረውም ይህ ታሪካዊ ስምምት ለሀገራችን ትልቅ ስኬት በመሆኑ ታላቅ ደስታ የሰማቸው መሆኑን በመግለጽ፣ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርና ሎጅስቲክስ አመራር እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ https://www.facebook.com/ethiopian.esl?__cft__%5b0%5d=AZVIXEtrKIMPBU2L-SQ-53XXaflDhKM2F4ge1PhH8lAbC8vbR9YCs3Cap5uX-XD9QNtESfcpLfBo6jrluvBtrjdrNbVvB8ZYtU7vghqERF5wNukog1npooYiiEMKext3XSHx8mZ9xkF-dIastmEbSnlfmzSI8jKwD-LP1M_KHHAmyFYb2ak145pDhnBmOrf0V3jcriR_oRRKlU_BCoixsrpr&__tn__=-UC%2CP-R
Leave a Comment