የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ መስራ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ መስራ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮችዛሬ በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ተገኝተው ውይይት ባደረጉበት ወቅት ሁለቱም የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንደመሆናቸው የሀገርን ኢኮኖሚ በሚያገዝፉ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል በሚፈጥሩና የሎጀስቲክስ ዘርፉን ገቢ በሚያልቁ ጉዳዮች ላይ በአብሮነት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ እና በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍስሃ ይታገሱ (ደ/ር) የተመራው ይኸው የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ተገኝቶ የሎጀስቲክስ የመሰረተ ልማት ስራዎችንና የማስፋፊያ ግንባታውን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት እንደ ዜጋ ክብር የተሰማቸው እና የሀገራችን ብልጽግና አይቀሬ ስለመሆኑ የተገነዘቡበት እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላ ከሁለቱም ድርጅቶች በአብሮነት ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመነሻ የመወያያ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በተለይ በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል በቀረበው መወያያ በድሬዳዋ ወደብና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ዞን መካከል ባለው 500 ሄክታር ቦታ ላይ በጋራ ማልማት ቢቻል ለ 100 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚቻል ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡ በኢባትሎ በኩል በቀረበው የመወያያ ጽሑፍም በኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አምራች ድርጅቶች በአስመጪነትም ሆነ በላኪነት ከኢባትሎ ጋር ለሚሰሩ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች መዘጋጀታቸውን ገልፀው የአብሮነት ስራው የአምራቾቹን ስራ ውጤታማ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር አምራቾቹ ዘንድ ሀገር ልታገኝ የሚገባትን የሎጀስቲክስ ዘርፍ ጥቅም አሟጣ እንድትጠቀም ሊያደርግ እንደሚችል በማንሳት አይ ፒ ዲ ሲ ም የአብሮነት ስራው እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተጠይቋል፡፡ በሁለቱም የልማት ድርጅቶች በኩል የቀረበውን የመወያያ ጽሑፍ መነሻ በማድረግ በከፍተኛ አመራሩ ደረጃ የቀረቡትን ሃሳቦች ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንዲቻል የጋራ ኮሚቴ ኮሚቴ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሶ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ኮሚቴው በየጊዜው የደረሰበትን ለከፍተኛ አመራሩ እያቀረበ እንዲያሰገመግም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡