የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመጨመር ለደንበኞቹ ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ያውቃሉ?

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመጨመር ለደንበኞቹ ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ያውቃሉ? የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከዚህ ዓመት ጀምሮ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ወደ ሩቅ ምስራቅ ሀገራት ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ ወደሚገኙ ወደቦች አዳዲስ የጉዞ መስመር በመክፈት ለደንበኞቹ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ድርጅቱ የራሱን 10 መርከቦች በመጠቀም ከአሁን ቀደም በመደበኛነት ከሚሰማራባቸው ከቻይና፣ ህንድና ገልፍ አገራት ከሚገኙ መዳረሻ ወደቦች በተጨማሪ አዳዲስ የንግድ መዳረሻ ወደቦችን መጨመሩ ለደንበኞቹ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡ የድርጅቱ መርከቦች የተለያዩ የጭነት ዓይነቶችን የመጫን አቅም ያላቸው (Multi-Purpose) በመሆናቸው በዋናነት ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ሌሎች ገቢ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ምቹ፤ ለደንበኞች ተመራጭ እንዲሁም በጊዜ እና በወጪ ረገድም ተወዳዳሪ የለሾች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የገበያ ፍላጎትን እና የአዋጭነት ጥናትን መሠረት ያደረገ አዳዲስ መዳረሻ ወደቦችን በመክፈት አገልግሎቱን የማስፋት ዕቅድ እንዳለው ስናሳውቅዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ Beyond The Sea!